Fana: At a Speed of Life!

ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተ ተመድ ያወጣው መግለጫ መሰረተ ቢስ ነው – የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ መሰረተ ቢስ ነው ሲል የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተ ትናንት ያወጣው መግለጫ ተቀባይነት የለውም ሲል የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ሪፖርቱን መሰረተ ቢስ ብሎታል፡፡

ኤጀንሲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ልዩ ዘጋቢ በዶክተር ሞሀመድ አብዱሰላም ከሱዳን የወጣው መግለጫ ፍፁም የተሳሳተ፣ የኢትዮጵያን ሚና ዝቅ ያደረገ፣የግል ስሜት የተጫነው አስተያየት ነው ሲል ኮንኖታል።

ኢትዮጵያ ለዘመናት ስደተኞችን ተቀብላ ከለላ በመስጠት የምትታወቅበትን መልካም ስም የሚያጠለሽ ነው ብሎታል፡፡

ሚዛናዊነት የጎደለው መግለጫው፥ አሸባሪው የህወሃት ቡድን የፈፀመውን የወንጀል ድርጊት ከኢትዮጵያ መንግስት መልካም ተግባር የለየ አይደለም ብሏል።

መግለጫው አሸባሪው ህውሃት እኩይ ተግባርን ያልተመለከተ፤በመጠለያ ጣቢያዎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ፣ ጠለፋ፣ ዝርፊያና ከባድ መሳሪያ አጥምዶ የሚፈጥረውን ሽብር አይቶ እንዳላየ ማለፉን ኤጀንሲው ገልጿል።

ኤጀንሲው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የወጣውን መግለጫ አጣጥሎ ፤ ኢትዮጵያ ለስደተኞች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብሏል በምላሹ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.