Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን በድምፃቸው ማን ሊያስተዳድራቸው እንደሚገባ በመወሰናቸው ማንም የሚያስቀምጥላቸውን አሻንጉሊት መንግስት አይቀበሉም – ከንቲባ አዳነች አበቤ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን ማን ሊያስተዳድራቸው እንደሚገባ በቅርቡ ባካሄዱት ምርጫ በድምፃቸው በመወሰናቸው፣ ማንም የውጭ ሃይል የሚያስቀምጥልን አሻንጉሊት መንግስት ሊኖር አይችልም ሲሉ ምክትል ከንቲባ አዳዳነች አበቤ አስገነዘቡ።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች አሸባሪው የትህነግ ቡድን በማውገዝ የሀገር አንድነትን ለመጠበቅ የዘመተውን የመከላከያ ሃይል በመደገፍ ባካሄዱት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ባደረጉት ንግግር መከላከያ ሰራዊታችንና መላው የፀጥታ ሃይላችን የሀገራችንን ሉዓላዊነትና ክብር ለመጠበቅ እየከፈሉ ያሉት ተጋድሎ እንዲጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት እያሰሙ ያሉት ድምጽ ለሀገር ሉዓላዊነት፣ ክብርና ነፃነት የሚሰማ የሚሊዮኖች ድምፅ በመሆኑ ሊከበር እንደሚገባ ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ይህ የምናሰማው የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የጀግንነት ድምጽ አገር አፍራሽና የእናት ጡት ነካሽ የሆነው ከሃዲው ጁንታ አገራችንን ለማፍረስ የሚያደርገውን ሙከራ በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣውን ማንኛውም ፀረ ኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነት በጥብቅ ለማውገዝ የሚሰማ የሚሊዮኖች ድምፅ መሆኑንም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ በመስጠት ሰፊና ትዕግስት አስጨራሽ ትግል ሲያካሂድ መቆየቱን ያስታወሱት ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ÷ በመላው ህዝብ ትግል ከስልጣን የተወገደውን አሸባሪውን የህወሃት ጁንታ ከሞተበት ለማንሳት የሚጥሩ የውጭ ጣልቃ ገቦች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡና እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ ጠይቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.