የሀገር ውስጥ ዜና

በአንድ መድረክ ከ140 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ተሰበሰበ

By Meseret Awoke

August 08, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በአንድ መድረክ ከ140ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡

ከምሽቱ 10 ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት በዘለቀው የኢትዮጵያውያን የዳላስ አብሮነት ምሽት የአጋርነት መልዕክቶችን በማስተላለፍ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ መሰብሰቡን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገልጸዋል፡፡

በዚህም ድጋፍ በማሰባሰብ አዲስ ክብረ ወሰን መመዝገቡን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡

ድጋፉ እንዲገኝ ላስተባበሩ ለኮሚቴው ሰብሳቢና አመራሮች፣ ለኃይማኖት አባቶች፣ ለመድረክ መሪዎች እንዲሁም በጨረታ ጭምር በተደጋጋሚ የለገሱ አካላትን አምባሳደር ፍጹም አመስግነዋል፡፡

በቀጣይ በዳላስ የሚኖሩ ወገኖች ያደረጉትን ፈለግ በመከተል በሌሎችም ከተሞች የተጠናከረ የአጋርነትና የልገሳ ፕሮግራም እንደሚካሄድ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!