Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የተለያዩ የስራ ሃላፊዎችን ሹመት አፀደቀ።

ሹመቱን ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው 5ኛ የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ጉባኤው ነው ያጸደቀው።

በዚህ መሰረት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የፍትህና መልካም አስተዳደር ክላስተር ሃላፊ ሆነው ተሾመዋል።

ከዚህ ባለፈም ዶክተር ሰለሞን ኪዳነ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የትግራይ ከተሞች ክትትል ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን ከህውሓት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የአቶ አስመላሽ ወልደስላሴ የትግራይ ክልል በይነ መንግስታት ጽህፈት ቤት ሃላፊነት ሹመትም አጽድቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.