Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ግዛቶች ደን ላይ ከደረሱ የሰደድ እሳት አደጋዎች የካሊፎርኒያው በአስከፊነቱ 2ኛ ደረጃን ይዟል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ግዛት በሰሜን ካሊፎርኒያ ደን የተነሳው እና እየተባባሰ የመጣው የሰደድ እሳት አደጋ በሀገሪቷ ታሪክ ደን ላይ ከደረሱ የሰደድ እሳት አደጋዎች በ2ኛ ደረጃ ይቀመጣል ተባለ፡፡
እየተባባሰ በመጣው የሰደድ እሳት አደጋ ጋር ተያይዞ እስካሁን ሦሥት ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁ ነው የተገጸው፡፡
በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም አካባቢውን ለቀው በመሸሽ ላይ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
የተነሳው ሰደድ እሳት ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ 369 ሺህ በላይ ሄክታር ደን ማውደሙ ተነግሯል፡፡
ይህን ተከትሎም አደጋው አሁን ላይ በስፋቱ ከሎስ አንጀለስ ግዛት የሚበልጥ አካባቢ ማውደሙ ነው የተገለጸው፡፡
በአሜሪካ ደን ላይ ከደረሱ የሰደድ እሳት አደጋዎች በአስከፊነቱ የቀዳሚነት ደረጃ የያዘውበ2018 በሜንዶሲኖ ብሔራዊ ደን ላይ የተከሰተው አደጋ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ምንጭ ÷ ሲጂቲ ኤን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.