Fana: At a Speed of Life!

ህጻናት ወደ ጦርነት እየተማገዱ በመሞት ላይ ስለሚገኙ የትግራይ ህዝብ ለአሸባሪው መጠቀሚያ መሆን አይገባውም – ምርኮኞች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ምንም የማያውቁ ታዳጊ ህጻናትና ንጹሃን ዜጎች በግፍ ወደ ጦርነት እየተማገዱ በመሞት ላይ ስለሚገኙ የትግራይ ህዝብ ከዚህ በኋላ ለአሸባሪው መጠቀሚያ መሆን አይገባውም ሲሉ የአሸባሪው ህወሃት ምርኮኞች ገለጹ፡፡

ካልአይ መምበረ በፈንቲ – ረሱ ግንባር በተካሄደው ውግያ ቆስሎ የተማረከ ሲሆን÷ ከመቀሌ ከተማ ድንገት ታፍኖ ከታሰረ በኋላ የሶስት ቀናት ስልጠና ከተሰጣቸው መካከል አንዱ በመሆን ወደግንባር መምጣቱን ይናገራል።

በግንባር ሲገባም እሱን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሳሪያ ከመከላከያ ቀምተን እንሰጣችኋለን ብለዋቸው ያለመሳሪያ ወደ ጦርነት እንዳስገቧቸው ጠቅሶ÷፤ በዚህ ሂደት ለማምለጥ ሲሞክርም ተመቶ መያዙን ነው የገለጸው።

ወደ ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባ በዝቶብን ተሰቃይተን ነውም ብሏል።

ለአሸባሪው ቁንጮ አመራሮች የስልጣን ፍላጎት ማሳኪያ እድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሱ ህጻናትና ታዳጊዎችን በግፍ ወደ ለጦርነት እየማገዷቸው መሆኑም ነው የተገለጸው።

ሌላው ምርኮኛ አንገሶም ገብረስላሴ በመቀሌ ከተማ በአሽከርካሪነት ከሚሰራበት በግድ ታፍኖ በመወሰድ መሳሪያ የመፍታትና መግጠም ስልጠና ብቻ ተሰጥቶት ወደ ጦርነት ተገዶ መግባቱን ተናግሯል።

ውጊያው እንደተጀመረም አብረውት የነበሩ በርካታ ሰዎች ሞተውና ቁስለኛ ሆነው አይቶ በመደንገጥ ህይወቱን ለማትረፍ ለመሸሽ ሲሞክር ተመቶ እንደተያዘ ነው ያስረዳው።

የመከላከያ ሠራዊትና የአፋር ልዩ ሃይል ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በሰብአዊነትና ወገናዊነት በተሞላበት መልኩ እንክብካቤና ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን በመጥቀስ ምስጋና አቅርቧል።

ምንም የማያውቁ ታዳጊ ህጻናትና ንጹሃን ዜጎች በግፍ ወደ ጦርነት እየተማገዱ እየሞቱ ስለሚገኙ የትግራይ ህዝብ ከዚህ በኋላ ለአሸባሪው መጠቀሚያ መሆን አይገባውም ብሏል።

ክብሮም ገብረማሪያም ሌላኛው ምርኮኛ ሲሆን÷ ከመቀሌ ተይዞ በግዳጅ የአጭር ጊዜ ስልጠና ወስዶ ወደጦርነት መግባቱን መናገሩን የዘገበው ኢዜአ ነው።

አሸባሪው ቡድን የራሱን እድሜ ለማራዘም የድሃ ልጆችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች እየገፋ ወደ ጦርነት በማስገባት በአሰቃቂ ሁኔታ እያስፈጃቸው ነው።

የትግራይ ህዝብ ለአሸባሪዎቹ የስልጣን መጠቀሚያ መሳሪያ ከመሆን በመቆጠብ ቡድኑን በቃህ ሊለው እንደሚገባም ወጣቶቹ አመልክተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.