Fana: At a Speed of Life!

የቦረና ዞን አርብቶ አደር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የእርድ ሰንጋዎችንና ፍየሎችን አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦረና ዞን አርብቶ አደር ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ያለውን አጋርነት ለማሳየት ያበረከተውን 300 ፍየልና 59 የእርድ ሰንጋ ወደ ግንባር በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የቦረና ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሬባ ኦዳ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ከዞኑ አርብቶ አደር ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚደረገው የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ እንደቀጠለ ነው፡፡

እስካሁን ከተበረከተው መካከል 2 ሚሊየን 175 ሺህ ብር የሚገመት 300 ፍየልና 59 የእርድ ሰንጋ ሲሆን÷ ይህንንም ለመከላከያው ለማድረስ ጉዞ መጀመሩን ነው የገለጹት፡፡

ለህልውና ዘመቻው በዞኑ ሴቶች ብቻ በ150 ሺህ 500 ብር የሚገመት 19 ኩንታል ደረቅ ምግብ መዘጋጀቱንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የዞኑ ህዝብ በመጀመሪያው ዙር የህግ ማስከበር ዘመቻ ለመከላከያ ሰራዊቱ ስንቅ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማደረጉንም አቶ ሬባ አስታውሰዋል፡፡

“ሽብርተኛው ህወሀት በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የፈጸመው ጥቃት ሳያንስ አሁን ደግሞ ህጻናትን በማሰለፍ ሀገር ለማፍረስ የከፈተው ጦርነት የዞኑን ህዝብ አስቆጥቷል”ብለዋል፡፡

አርብቶ አደሩ ህብረተሰብ ሀገሩን ለሚከላከለው ሰራዊት የሚያደርገው ድጋፍ ቀጣይነት እንዳለውም አውስተዋል፡፡

በፍላጎትና ተነሳሽነት መከላከያ ሰራዊቱን በመቀላቀል ሀገር ለማደን ሙሉ ፍላጎት ላላቸው ፈቃደኛ ወጣቶች ሽኝት መደረጉንም አስታውሰዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.