የገናሌ ዳዋ III ኃይል ማመንጫ ጥር 26 ይመረቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 254 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የገናሌ ዳዋ III የውሃ ኃይል ማመንጫ ጥር 26 ቀን ይመረቃል።
የገናሌ ዳዋ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ 2 ነጥብ 57 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም አለው።
ለግንባታው 451 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገ ሲሆን፥ 60 በመቶው ከቻይናው ኤክዚም ባንክ በብድር እንዲሁም ቀሪው 40 በመቶው ደግሞ በመንግስት ወጪ የተሸፈነ ነው።