የሀገር ውስጥ ዜና

በሐረሪ ክልል በ19ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የተገነቡ የተለያዩ የጤና መሠረተ ልማቶች ተመረቁ

By Meseret Awoke

August 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሐረሪ ክልል በ19ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የተገነቡ የተለያዩ የጤና መሠረተ ልማቶች ተመርቀዋል፡፡

በክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦድሪን በድሪ የተመራ ልዑካን ቡድን በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙ የመሠረተ ልማት ስራዎችን ተዘዋዉሮ ጎብኝቷል።

ከተመረቁት መሠረተ ልማት ስራዎች መካከል በ12 ሚሊየን ብር የተገነባው የአውበርከሌ የመጀመሪያ ትውልድ ጤና ኬላ አንዱ ሲሆን÷ የህብረተሰቡን የዘመናት ጥያቄ ይፈታል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።

ፕሬዚዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ የሐረር ጤና ኮሌጅ በ8 ሚሊየን ብር የተገነባውን አጥር መርቀው የኮሌጁን የስራ ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የኮሌጁን የመማር ማስተማር ሂደት ለማሳለጥ ታስቦ በ95 ሚሊየን ብር እየተገነባ የሚገኘውን ባለ አምስት ወለል የመማሪያ ህንፃ የጎበኙት ፕሬዚዳንቱ÷ ህንፃው በተያዘለት ቀነ ገደብ እንዲጠናቀቅ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮች እንዲፈቱ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በፕሬዚዳንት ኦድሪን በድሪ የተመራው የልዑካን ቡድን አረንጓዴ አሻራውን በማሳረፍ ጉቡኝቱን አጠናቋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!