የሀገር ውስጥ ዜና

በጁባ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

August 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጁባና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከኤምባሲው ዲፕሎማቶች 965ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት በጁባ በተቋቋመው ኮሚቴ አማካይነት በተካሄደው የድጋፍ ማሰባሰብ ሥራ ነው ድጋፉ የተሰበሰበው፡፡

በዚህም በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ለሚቀርብላቸው ሃገራዊ ጥሪዎች በጎ ምላሽ ሰጥተዋል ተብሏል፡፡

ለዚህም በኢትዮጵያ የተፈናቀሉና የተጎዱ ዜጎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም ሚሲዮኑ ባቀረበው ጥሪ መሠረት ነዋሪዎቹ ላሳዩት ተነሳሽነትና ሃገር ፍቅር አምባሳደር ነቢል ማህዲ ምሥጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!