Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሸባሪው ህውሃት በአፋር ክልል ጊዜያዊ መጠለያ በነበሩ ዜጎች ላይ ባደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሸባሪው ህውሃት በአፋር ክልል ጊዜያዊ መጠለያ በነበሩ ዜጎች ላይ ባደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ሐዘን ገለጸ።
 
ክልሉ አሸባሪው ህውሃት በአፋር ክልል ጊዜያዊ መጠለያ በነበሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ ባደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ሐዘን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡
 
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል ፡-
 
የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሸባሪው የህውሃት ቡድን በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ በጋሊማኮ ጊዜያዊ መጠለያ በነበሩ ንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ በፅኑ ያወግዛል።
 
አሸባሪው የህውሃት ቡድን እኔ ያልመራኋት ሀገር መበታተን አለባት በሚል እያካሄደ ባለው ተግባር በደረሰበት ሁሉ ሀገር አፍራሽነቱን በተግባር እያሳየ ይገኛል።
 
በአፋር ክልልም 107 ህፃናትን፣ 89 ሴቶችን እና 44 አዛውንቶችን ህይወት የቀጠፈ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ያካሄደው አሸባሪው ህወሓት ድንገት በከፈተው በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ንፁሃን አርብቶ አደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው እንዲሁም በመጋዝን የነበረ የአስቸኳይ እርዳታ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ይታወሳል።
 
በመሆኑም የሀረሪ ክልል መንግስትና ህዝብም ለአፋር ክልል መንግስትና ህዝብ ጁንታውን ለመመከትና በወረራው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ በሚከናወነው ተግባራት አሰፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርግ ይገልፃል።
 
የክልሉ መንግስት በጭፍጨፋው ምክንያት ለደረሰው ሞት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።
ከዚህ ባሻገር በአሁኑ ወቅት መላው ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ይህን ፀረ ህዝብ አሸባሪ ቡድን እስከ መጨረሻው ለማጥፋትና ሀገርን ለማዳን እያደረጉት ያለው ርብርብ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።
 
አሸባሪው ህውሃት በብሔር ብሔረሰቦች ትብብር ይወገዳል!
 
ኢትዮጵያም በልጆቿ ጥረት ሉዓላዊነቷ ተከብሮ ለዘላለም ትኖራለች!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.