Fana: At a Speed of Life!

ወልድያን ለመቆጣጠር የመጣው አሸባሪው ሀይል በመደምሰስ ላይ ይገኛል- የመከላከያ ሰራዊት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ዕዝ የ21ኛ ጉና ክፍለጦር ወልድያን ለመቆጣጠር የመጣው አሸባሪው የጁንታ ሀይል በጉባላፍቶ ወረዳና አካባቢው በመደምሰስ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ እንደገለፁት÷ አሸባሪው ሃይልና ርዝራዦቹ ትላንት የመከላከያ ሠራዊት ያደረሠበትን ቅጣት በመዘንጋት ዳግም የቅዠት ህልሙን አሣካለሁ ብሎ ህፃናትን ወደ ጦርነት እየማገደ እንቅሥቃሤ ለማድረግ ቢሞክርም በ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት ሣንቃ በተባለውና በጉባላፍቶ ወረዳ አካባቢ የሽብር ቡድን አባላትን መደምሰስ ተችሏል።
ጁንታው ወልድያን ተቆጣጥሪያለሁ ያለውን ሀሰተኛ ወሬ በማሥታወስ በአሁኑ ሠዓት ወልድያ ላይ ሁነን እንኳን የሀሰት ወሬውን በመንዛት ይህንን አካባቢ ተቆጣጥሪያለሁ እያለ ህዝብን የሚያሸብር ተግባሩን እንደ አንድ የጦርነት ሥልት እየተጠቀመበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም ህዝቡ በአሸባሪው “የበሬ ወለደ”ወሬ ሣይደናገርና ሣይረበሽ ከሠራዊቱ ጎን በመሆን ህዝባዊ ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ።
የ21ኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት አሁንም በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ መሆኑን አዛዡ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.