Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የህወሓት ባንዳ በአፋርም ሆነ በሌሎች የሃገሪቱ ህዝቦች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት የሚቆመው በጋራ ክንድ ሲደመሰስ ብቻ ነው-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአፋር ህዝብ አጋርነት መግለጫ አውጥቷል፡፡
መስተዳድሩ የሰጠው ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪው የህወሃት ባንዳ ቡድን በእብሪት በከፈተብን ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው በአንድ አፋር ክልል በመጠለያ ጣቢያ በተጠለሉ 240 ሰላማዊ ዜጎች ላይ ልብ የሚሰብር ጥቃት ፈጽሟል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራርና መላ ነዋሪዎች አሸባሪው ሃይል በሰነዘረው የጭካኔ ጥቃት ህይወታቸውን ለጡ ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል።
በዚህ አጋጣሚም ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለአፋር ህዝብና መንግስት መጽናናትን እንመኛለን።
የአፋር ህዝብ የአሸባሪው ሃይል የጥቃት ሰለባ የሆነው ሀገሩን ከመፍረስ ለመታደግ በጀግንነትና በጽናት በመቆሙ ነው።
ኢትዮጵያን ከራሱ ጠባብ ፍላጎት አስበልጦ ማየት የማይችለው የህወሓት አሸባሪ ቡድን ሰሞኑን የአፋርን መስመር በመስበር ሀገራችንን ከጂቡቲ የሚያገናኘውን መንገድ ለመዝጋት ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጓል።
ይሁን እንጂ ሙከራው በአይበገሬዎቹ የአፋር ልዩ ሃይሎችና ሚሊሻ ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጋር በመቀናጀት ባካሄዱት ውጤታማ የመከላከልና መልሶ ማጥቃት ትርጉም ባለው ደረጃ ከሽፏል።
የአፋር፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎቻችን ባደረሱበት ኪሳራ ክፉኛ የተበሳጨው ሀገር አፍራሹ የህወሃት ባንዳ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ የብቀላ እርምጃ የወሰደው ፊት ለፊት በሚፋለመው የሰራዊታችን ካምፕ ላይ ሳይሆን ከጦርነት ጥቃት ሸሽተው መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ ነው።
በከባድ መሳሪያ ጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ተፈናቃዮች መካከልም አብዛኛዎቹ ሴቶችና ህጻናት ናቸው።
አሸባሪው ሃይል የትግራይ ህጻናትን እያስገደደ በማስታጠቅ በጦርነት እሳት እንዲለበለቡ ማድረጉ ሳያንሰው ከጦርነት ሸሽተው መጠለያ ውስጥ በሚገኙ ንጹሃን ዜጎቻችን ላይ ያደረሰው ጭፍጨፋ ኢ.ሰብዓዊነቱንና ህዝብ ጠልነቱን ዳግም ያረጋገጠበት እውነታ ነው።
አሸባሪው የህወሓት ባንዳ በአፋርም ሆነ በሌሎች የሃገራችን ህዝቦች ላይ የሚያደርሰው ጭፍጨፋ፣በደልና ጉዳት የሚቆመው በመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች የጋራ ክንድ ተጠቃሎ ሲደመሰስ ብቻ ነው።
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር አምባገነናዊ አገዛዝ በመትከል የጥቂቶችን ስግብግብ ፍላጎት እያሟላ ለመኖር የሚሻው ይህ የጥፋት ሃይል ዛሬ በእኛ መስዋዕትነት ካልተነቀለ ቀጣዩን ትውልድ ሲያስለቅስ የሚኖር ነቀርሳ ነው።
እናም የአፋር ህዝብና መንግስት ዛሬ የደረሰባችሁ የልብ ስብራት ሀገራችሁን ከመፍረስ ፤ልጆቻችሁን ዕድሜ ልክ ከማልቀስ የሚያድን ክቡር መስዋዕትነት መሆኑን ተገንዝባችሁ አሸባሪውን በመስበርና በመቅበር ዘመቻው ውስጥ እስካሁን ላሳያችሁት የጽናትና የጀግንነት መንፈስ ያለንን አድናቆትና አክብሮት እንገልጻለን።
የከተማ አስተዳደራችና መላው ህዝባችን ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ በሁሉም መልክ ከጎናችሁ እንደማይለይም በዚህ አጋጣሚ ያረጋግጥላችኃል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.