Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ካሊጎማ የእርዳታ እህል ወደቦታው መንቀሳቀስ ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ካሊጎማ አሸባሪው ህውሃት ላስከተለው ቀውሰ የተነሳ ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ሰዎች የሚውል የእርዳታ እህል ወደቦታው መንቀሳቀስ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገለጸ።
አሸባሪው ህወሃት በአፋርና በአማራ ክልል በንፁሃ ላይ ባስከተለው ቀውስ 300 ሺህ ሰዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡
መንግስት አሁን ላይ እያካሄደ ያለው ዘመቻ በትግራይ ክልል መሽጎ በሚገኘው አሸባሪ ቡድን ላይ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል።
መንግስት ለመላው ህዝብ ጥሪ ያደረገው ዜጎች አካባቢያቸውን ማህበረሰባቸውን ነቅተው እንዲጠብቁ እና መከላከያው ሌሎች ድንገተኛ ጥሪዎችም ስላለበት መሆኑን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወደ ትግራይ እስካሁን 277 እርዳታ የጫኑ መኪኖች መግባታቸውንም አስታውሰዋል።
የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሃትን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ወደ ማድመጡ ማዘንበሉን የፕሬስ ሴክሬቴሪያት
ሃላፊዋ ጠቁመዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.