Fana: At a Speed of Life!

በበጀት ዓመቱ ለጎረቤት ሀገራት ከተሸጠ የኤሌክትሪክ ኃይል ከ90 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው የ2013 በጀት ዓመት ለጎረቤት ሀገራት ከተሸጠ የኤሌክትሪክ ኃይል ከ90 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
በበጀት ዓመቱ ለሱዳን እና ጅቡቲ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ 80 ነጥብ 7 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ ኤሌክትሪክ በማቅረብ 90 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መሰብሰቡን መምሪያው አስታውቋል፡፡
ይህም ከእቅዱ የ9 ነጥብ 7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም የ12 በመቶ ብልጫ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡
ወደ ሀገራቱ በተናጠል ለሱዳን 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ በመሸጥ 55 ነጥብ 48 ሚሊየን ዶላር እንዲሁም ለጅቡቲ ከ5 መቶ 27 ሚሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ በመሸጥ 35 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡
ተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከውጭ ሃገራት የኃይል ሽያጭ የሰበሰበው ገቢ በ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከሰበሰበው ጋር ሲነፃፀር የ24 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም የ36 ነጥብ 2 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
በ2013 በጀት ዓመት ለኬንያ 695 ሚሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ 48 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በኬንያ በኩል እየተገነባ ያለው የኢትዮ-ኬንያ የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ግንባታ ባለመጠናቀቁ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ አልተቻለም ተብሏል፡፡
ተቋሙ ከውጭ ሃገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የሚሰበስበው ዓመታዊ ገቢ በየዓመቱ እያደገ የሚገኝ ሲሆን፥ ይህም 2011 በጀት ዓመት ከነበረበት 54 ነጥብ 9 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በ2012 በጀት ዓመት 66 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያደገ ሲሆን፥ በ2013 በጀት ዓመትም 90 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መድረስ መቻሉን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡
የኃይል ማመንጫ ግድቦች በቂ ውሃ መያዛቸው እና የኃይል መቆራረጥ መቀነሱ ለበጀት ዓመቱ እቅድ መሳካት እና በዓመቱ ለተስተዋለው የገቢ አሰባሰብ እድገት በምክንያትነት መጠቀሳቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.