Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ቡድን የትግራይ ሴቶች እና ህፃናትን ያለምንም ወታደራዊ ስልጠና ለጦርነት እየማገደ ነው – ምርኮኞች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን የትግራይ ሴቶች እና ህፃናትን ያለምንም ወታደራዊ ስልጠና ለጦርነት እየማገደ መሆኑን በአፋር በኩል በመከላከያ ሰራዊታችን የተማረኩ የቡድኑ ታጣቂዎች ተናገሩ።

የሽብር ቡድኑ እድሜአቸው ለውትድርና አገልግሎት ብቁ ያልሆኑ ህፃናት እና ሴቶችን ከቀዬአቸው በተሳሳተ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማስገደድ ለእንግልት እና ለጦርነት አደማገደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ያለምንም ወታደራዊ ስልጠና ወደ አፋር ክልል ሰርገው በመግባት በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥፋት ሊያደርሱ ሲሉ በጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

ሽብርተኛ ቡድኑ አስገድዶ ላሰማራቸው ታጣቂዎቹ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ስ፤ልሃገር መከላከያ ሰራዊት ፍፁም የሆነ ጥላቻ እና የተዛባ ትርክት እንደተነገራቸው የገለፁ ሲሆን÷ ስለሚዋጉበት ዓላማም ሆነ ሌላ ጉዳይ ጥያቄ ማንሳት የማይቻል መሆኑን ተናግረዋል።

ሰራዊቱ በመንግስት ውሳኔ መሰረት ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ አሸባሪው ትህነግ ወደ ክልሉ በመግባት ሰራዊቱን እንደደመሰሰ በማስመሰል ለቅስቀሳ የሚጠቀምበት መሆኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አሸባሪው ቡድን በሚሰጣቸው አደንዛዥ እፆች አማካኝነት በጦርነቱ የቆሰሉ ምርኮኞች የደረሰባቸውን ጉዳት መገንዘብ አለመቻላቸውንም ነው የገለጹት።

ሽብርተኛው ህወሃት በአሁኑ ሰዓት አስገድዶ ላሰማራቸው ታጣቂዎች አንድ መሳሪያ ለስድስት ሰው እያስታጠቀ በመሆኑና ምንም አይነት ሎጀስቲካዊ ድጋፍ ማቅረብ የማይችል በመሆኑ ታጣቂዎቹ በርሃብና በእንግልት ምክንያት ምንም አይነት የመዋጋት አቅም እንደሌላቸው አብራርተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.