Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ጀማል በከር ከባህሬን የኢንዱስትሪ ንግድና ቱሪዝም ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህሬን የኢትዮጵያ ቆንስል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አምባሳደር ጀማል በከር ከባህሬን የኢንዱስትሪ ንግድና ቱሪዝም ሚኒስትር አቶ ዜይድ አልዜይን ጋር በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ አምባሳደር ጀማል በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ የህግና የአሰራር ማበራታቻዎች ዙሪያ በተለይም በግብርና፣በማኑፋክቻሪንግ፣አግሮፕሮሰሲንግ፣ በኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣በቱሪዝምና አገልግሎቶች መስክ ያሉትን ዕድሎች በተመለከተ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
የግብርና፣የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦና የአግሮፕሮሳስንግ ምርቶች በባህሬን ገበያ በሚቀርቡበት ሁኔታ ዙሪያም ተዋያይተዋል፡፡
አያይዘውም አምባሳደር ጀማል ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡
አቶ ዜይድ አልዜይን በበኩላቸው÷ የሁለቱ አገራት የኢንቨስመንት፣ የንግድና የቱሪዝም ትስስር እንዲጠናከር እና የኢትዮጵያ የግብርና፣ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች በባህሬን ገበያ እንዲገቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን እንዲጐበኙ የቀረበውን የግብዣ በመቀበል የፈረንጆች አመት ከመጠናቀቁ በፊት ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሃብቶችንና የኩባንያ ኃላፊዎች በመያዝ ጉብኝት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.