Fana: At a Speed of Life!

ራዕይ ለተጋሩ ኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ህዝባዊ ንቅናቄ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ተወላጆች አማካኝነት ራዕይ ለተጋሩ ኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ህዝባዊ ንቅናቄ ተመሰረተ።

የህዝባዊ ንቅናቄውን ምስረታ በማስመልከት በዛሬው እለት አስተባባሪዎቹ  መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ሊላይ ሃይለማርያም በመግለጫው ላይ እንደገለጹት፥ በተወሰኑ የአድዋ ገዥ መደቦች የትግራይ ህዝብ እየተበደለ ይገኛል።

የትግራይ ህዝብ ላለፉት ሶስት ሺህ አመታት ለሀገረ መንግስት ግንባታ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር የራሱን አሻራ ያስቀመጠ ህዝብ ነው ያሉት አቶ ሊላይ፥ በአሁኑ ወቅት ትግራይን ለመገንጠል አስበው ሳይሳካላቸው በቀሩ ለህዝብ በማይጠቅሙ ቡድኖች መጠቀሚያ ሊሆን አይገባም ብለዋል።

አቶ ሊላይ በመግለጫው እንዳስታወቁት፣ የንቅናቄው አላማም እነዚህ የትግራይን ህዝብ በተሳሳተ መንገድ ባይተዋር እንዲሆን እየሰሩ ያሉ ሀይሎችን ለመመክት ያለመ ነው።

ሰለሆነም በአሁኑ ሰአት በትግራይ የሚካሄደው ጦርነት የአንድ ቡድን እኩይ አላማን ለማሳካት መሆኑን አውቆ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው የትግራይ ህዝብ በቃችሁ ሊላቸው ይገባል ብለዋል።

ህወሃት በትግራይ ህዝብ ላይ ስፍር ቁጥር የሌለው በደል አድርሷል ያሉት አቶ ሊላይ፤ አሁንም ለ27 አመት የሰራው በደል አልበቃው ብሎ ህዝቡን ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል።

ንቅናቄው በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ተጋሩን በማደራጀት የሚሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.