Fana: At a Speed of Life!

የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውሃ አካባቢ ተደመሰሰ- የመከላከያ ሰራዊት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከሃዲው በቀድሞው የ31ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራው የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውሃ አካባቢ መደምሰሱን የመከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡

በዚህ ውጊያ ከ70 በላይ የጠላት ሃይል ሊደመሰስ ችሏል ፡፡

ክፍለ ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ በወገን ጦር ላይ ጥቃት ለማድረስ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረውንና በከሃዲው ጀነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራውን የጠላት ጦር በአስደናቂ የወታደራዊ ስልት መደምሰስ መቻሉን የ211ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ እና ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል አስታውቀዋል።

አዛዦቹ እንዳስታወቁት በሰራዊቱ አባላት እልህና ቁጭት አስደናቂ የጀግንነት ተግባር ተፈፅሟል።

ክፍለ ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ በፈፀመው የጀግንነት ውሎው ከ70 በላይ የጠላት ሃይል ሲደመሰስ ፣ 19 ክላሽን ኮቭ መሣሪያ ፣ 5 ስናይፐር እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ከከባድ እስከ ቀላል የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል ።

ሠራዊቱ አሁንም የህልውና ዘመቻውን በአስተማማኝ የጀግንነት መንፈስ ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.