Fana: At a Speed of Life!

የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከ450 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበትን በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካን በዛሬው ዕለት መርቀዋል።

የሕክምና ኦክስጂን ማምረቻ ፋብሪካው በሰዓት 270 ሚሊ ሜትር ኪዩብ ኦክስጅን የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ከ500 በላይ አልጋዎች ላሉት ጥበበ ጊዮን ሆስፒታል የሕክምና ኦክስጂን እንዲያመርት የተገነባው ፋብሪካው ከዚህም አልፎ ለሌሎች የሕክምና ተቋማት በቀን እስከ 300 ሲሊንደር ኦክስጅን ማምረት የሚያስችል አቅም አለው ተብሏ፡፡

የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከሉ በክልሉ በሚገኙ ጤና ተቋማት በኦክስጅን እጥረት የሚሞቱ ሰዎችን ሕይወት ለመታደግ እገዛው የጎላ ነው መባሉን መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.