Fana: At a Speed of Life!

የካናቢስ እፅ ይዛ የተገኘችው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የካናቢስ እፅ በማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ ይዛ የተገኘችው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣች፡፡
ተከሳሽ መቅደላዊት ገዛኸኝ ግርማ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 525/2/መ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በቀን 29/06/2012 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቃሊቲ የፌዴራል ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ በቢጫ ኩርቱ ፌስታል የምግብ ላስቲክ ሳህን ውስጥ በቀይ ስጋ ወጥ ተሸፍኖ የተሰፋና በውስጡ በላስቲክ የተጠቀለለ 15 ጥቅል የሆነና በአጠቃሊይ 18 ግራም የካናቢስ ዕፅ ይዛ ተገኝታለች።
በመሆኑም እንዳይዘዋወርና በጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከለን ዕጽ ማዘዋወር ወይም ይዞ መገኝት ወንጀል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት በዐቃቤ ህግ ክስ ቀርቦባታል፡፡
ተከሳሽ ችሎት ቀርባ የእምነት ክህደት ቃሏን ስትጠየቅ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዳ በመከራከሯ ዐቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ ያስረዳ ሲሆን ፥ እንድትከላከል ችሎቱ ብይን ቢሰጥም ተከሳሽ መከላከል ባለመቻሏ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች በሰጡት ቃል መሰረት ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል፡፡
በዚህም ተከሳሽ 7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እና በ2 ሺህ 500 ብር መቀጮ እንድትቀጣ መወሰኑን ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
No photo description available.
9
People Reached
313
Engagements

-3.4x Lower

Distribution Score
Boost Post
122
5 Comments
4 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.