Fana: At a Speed of Life!

ኩባ ላደረገችው የሰብዓዊ ድጋፍ ኢትዮጵያ አመሰገነች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኩባ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ በኩባ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ አመሠገኑ።

አምባሳደሩ የኩባና የኢትዮጵያ ግንኙነት ጠንካራ መሰረት ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኩባ በ1970 ዎቹ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ ተሳታፊ ሆና ታሪክ የማይረሳው እና በደም የተፃፈ ጀብድ መፈጸሟን አስታውሰው÷ በምክር ቤቱም ያሳየችው ድጋፍ ይሄንኑ የጋራ ታሪክ የሚያስታውስ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

አምባሳደሩ የኩባ እና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ትብብር በጤና ፣ በትምህርት ፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሌሎች በርካታ መስኮች ላይ ለዓመታት ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ስምንት ወራት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከአካባቢው ለማስወጣት የተቻለውን ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ፣ በአጥፊው ቡድን በአፋር እና አማራ ክልሎች የወደሙትን መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡

አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሰላማዊ ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋና የንብረት ዘረፋመፈጸሙንም አስታውሰው÷ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረገውን የምግብ ድጋፍ እንዳይደርስ እንቅፋት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሁለተኛው የውሃ ሙሌት በተፋሰሱ ሃገራት ላይ ተጽእኖ ሳያደርስ መሞላቱን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፡- ፕሬንሳ ላቲና

ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.