Fana: At a Speed of Life!

በህወሃት ሴራ አጎራባች አካባቢ የምንኖር ህዝቦች ስንጋጭ ኖረናል-አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከዚህ በፊት በህወሃት ሴራ አጎራባች አካባቢ የምንኖር ህዝቦች ስንጋጭ ኖረናል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ ።

የሲዳማ ክልል ሠላምና ፀጥታ ሴክተር ከኦሮሚያና ደቡብ ክልል አጎራባች ዞኖችና የወረዳ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ የሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በሀዋሳ ከተማ እየመከረ ይገኛል።

በውይይት መድረኩ የሲዳማ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ፥ በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በወሰን የምንገናኝ ክልሎችና ዞኖች ተገናኝተን መወያየታችን ለሀገራችን ያለንን ፍቅርና አንድነት ያሳያል  ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው ፥ አሁን ያለንበት ወቅት ሀገራችን ለኛ እኛም ለሀገራችን በእጅጉ የምናስፈልግበት ወቅት ላይ ነው ብለዋል።

ባለፉት 27 ዓመታት  አሸባሪው ህወሃት የኢትዮጵያን ህዝብ በግፍ ሲያስተዳድር ቆይቶ ከተወገደ በኋላ አሁን ተመልሶ ለኢትዮጵያ ጠላት ሆኗል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በብሔር፣ በቋንቋና በሃይማኖት ሊለያየን  ሲሰራ  ቆይቷልም  ነው ያሉት።

አሸባሪ ቡድኑ የኢትዮጵያን እድገትና አንድነት ከማይወዱ የውጭ ሀይሎች ጋር በመሆን እየተዋጋ ይገኛል ብለዋል።

ከዚህ በፊት በህወሃት ሴራ አጎራባች አካባቢ የምንኖር ህዝቦች ስንጋጭ ኖረናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ከለውጡ ወዲህ ግን ያ ግጭት ጠፍቶ በአብሮነትና በወንድማማችነት ተሳስረን እየኖርን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ ፍቅራችን ወደፊትም መቀጠል አለበትም ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ።

በመድረኩ የኦሮሚያ፣ የሲዳማ እና የወላይታ አጎራባች ዞኖች የአገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የመንግስት የጸጥታ መዋቅር አካላት  ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በታምራት ቢሻዉ እና ተመስገን ቡልቡሎ

ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.