Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለመከላከያ ሰራዊት 55 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 55 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የድርጅቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ከወር ደመዛቸው ከ15 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ÷ድርጅቱ በበኩሉ 40 ሚሊየን 164 ሺህ 600 ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
በአጠቃላይ ከሰራተኞችና ከአመራሮች የደመወዝ መዋጮ እና ከድርጅቱ 55 ሚሊየን 964 ሺህ 600 ብር ለመከላከያ ሰራዊቱ ገቢ መደረጉን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሰራተኞቹ የመከላከያ ሠራዊት የጥፋት ኃይሎችን ለማንበርከክ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ እንደሚደግፉና የሚጠበቅባቸውን ድጋፍና ትብብርም እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

 

ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.