Fana: At a Speed of Life!

ሕብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጎን ቆሞ እየታገለ ነው – የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕብረተሰቡ የህወሓት ሽብር ቡድንን ለመደምሰስ ከፌደራል፣ ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች እና ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ዲኒ÷ህወሓት በጋሊኮማ የጊዜያዊ መጠለያ ካምፕ ላይ ሳይቀር በከባድ መሳሪያ ጥቃት በመፈጸም የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፉን አስታውሰዋል፡፡

የክልሉ ነዋሪዎች ጁንታውን ለመደምሰስ እያደረጉ ያለው ተሳትፎ የሚያኮራ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

በእስካሁኑ የድል ጉዞዎች በጁንታው የጦር ሎጀስቲክ እና የሰው ኃይል ላይ ጉዳት መድረሱን ያነሱት ኮሚሽነሩ÷ ከግንባር ባለፈ ህዝቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ ነው ብለዋል፡፡

ወጣቱ የክልሉን ልዩ ኃይል በመቀላቀል እና አካባቢውን በመጠበቅ በኩል እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

 

በጥበበ ስላሴ ጀምበሩና አወል አበራ
ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.