በኮሮና ቫይረስ በመያዝ የተጠረጠሩ አራት ኢትዮጵያውያን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ተረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሮና ቫይረስ በመያዝ የተጠረጠሩ አራት ኢትዮጵያውያን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ኢትዮጵያውያኑ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ በተደረገላቸው ምርመራ ነፃ መሆናቸው የተረጋገጠ ቢሆንም ለተጨማሪ ምርመራ ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ መላኩ ይታወሳል።
በዚህም በደቡብ አፍሪካ በተደረገው ምርመራ አራቱም ኢትዮጵያውያን ከኖቭል ኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል ብሏል ሚኒስቴሩ።