Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር  ቤንያሚን ኔታንያሁ በዛሬው ዕለት በሩሲያ ሞስኮ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞስኮ ቆይታቸውም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ መምከራቸው ነው የተገለጸው።

ከዚህ ባለፈም የአሜሪካው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ትራምፕ ይፋ ባደረጉት የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ ዙሪያ መወያየታቸው ተነግሯል።

በዚህ ወቅትም ኔታንያሁ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሰላም እቅዱ ዙሪያ ያነጋገሯቸው የመጀመሪያ መሪ መሆናቸውን በመጥቀስ፥ በጉዳዩ  ላይ ያላቸውን ሃሳብ እንዲያካፍሏቸው ጠይቀዋል።

ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ፑቲን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት መቆጠባቸው በዘገባው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል  መሪዎቹ በሩሲያ አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወር ወንጀል ተከሳ እስር ላይ የነበረች እስራኤላዊት በነፃ እንድትለቀቅ መስማማታቸው ተገልጿል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.