የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ በቱርክ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቀረቡ

By Melaku Gedif

August 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ጋር የነበረንን ውድ ጊዜ አጠናቀን ወደ ሀገር ተመልሰናል ብለዋል።

የቱርክ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን ኢትዮጵያ መቼም አትረሳውምም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትናንትናው እለት በቱርክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው መመለሳቸው ይታወሳል።

በወቅቱም በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል የተለያዩ የትብብር ስምምነቶች ተፈርመዋል።

ሃገራቱ በወታደራዊና በውሃ ዘርፍ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነቶች መፈራረማቸውም የሚታወስ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!