Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት የህወሓት ቡድን ላይ በተወሰደ እርምጃ ጀብዱ ተፈጽሟል – የአማራ ክልል መንግስት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ላይ በተሰወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ታላላቅ ጀብዱዎች መፈጸማቸውን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገለፁ።

ዋና ዳይሬክተሩ በሰጡት መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት በወልድያና አካባቢው፣ ጋይንትና አካባቢው፣ ዛሪማና አካባቢው፣ ሰቆጣና አካባቢው፣ ጋሸናና አካባቢው በህወሓት የሽብር ቡድን ላይ በተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ታላላቅ ጀብዱዎች መፈጸማቸውን ተናግረዋል።

በዚህም የሽብር ቡድኑ የደረሰበት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ከባድ መሆኑን መግለጻቸው ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ይህ ሆኖ ሳለ የማህበረሰብ አንቂዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በማህበራዊ ተስስር ገፆች የህወሓት የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲታቀቡ አቶ ግዛቸው አሳስበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.