Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ኘሬዚዳንት ጽ/ ቤት እና ሌሎች የክልሉ ቢሮ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ኘሬዚዳንት ጽህፈት ቤት እና ሌሎች የክልሉ ቢሮ ሰራተኞች “ህይወቱን ለሰጠን ሰራዊታችን ደማችንን እንሰጣለን” በሚል መሪ ቃል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሀግብር አካሂደዋል።
ደም ልገሳ መርሀ ግብሩን የኦሮሚያ ክልል ኘሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያዘጋጀ ሲሆን፥ በተጨማሪም ሌሎች የክልሉ ቢሮ ሰራተኞች በደም ልገሳ ተሳትፈዋል።
ከሰራዊቱ ጎን መሆናችንን ለማረጋገጥ ደም ለግሰናልያሉት ሰራተኞቹ፥ በቀጣይም ለመከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
በደም ልገሳ መርሃ ግብሩም ሰራተኞቹ እና የክልሉ አመራሮች መሳተፋቸውን ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የመከላከያ ሰራዊት አሸባሪው ህወሓት ሃገሪቷን ለመበተን የወጠነውን ሴራ ለማክሸፍ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው።
የህልውና ዘመቻው ፍሬ እንዲያፈራ መላው ህዝብ በገንዘብ፣ በዓይነትና በሞራል የሚጠበቅበትን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.