Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን እየተፋለመ ላለው የአገር መከላከያ ሠራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚህም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ከወር ደመወዛቸው 35 ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ መደረጉ ነው የተገለፀው፡፡
ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪም ዛሬ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች የደም ልገሳ አድርገዋል።
የሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማቱ ሠራተኞች የኢትዮጵያን አንድነት ለማስከበርና ሕዳሴዋን ለማረጋገጥ ከሽብርተኛው የሕወሓት ቡድን ጋር እየተፋለመ ላለው የሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውም ነው የተገለፀው፡፡
በተያያዘም የፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና የኮሪያ ዘማቾች ማህበር ለመከላከያ ሰራዊት የገንዘብ ድጋፍ አደርገዋል፡፡
የፈደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 17 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የኮሪያ ዘማቾች ማህበርም 40 ሺ ብር ነው የደገፈው፡፡
ድጋፉን የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ረሻድ ከማል ለመከላከያ የፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ያስረከቡ ሲሆን፣ በተመሳሳይ የኮሪያ ዘማቾች ፕሬዚዳንት ኮሮኔል እስጢፋኖስ ገብረመስቀል አስረክበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.