Fana: At a Speed of Life!

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በህልውና ዘመቻው ለተሰለፉ የሰራዊት አባላት ቤተሰቦች ነጻ የትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በህልውና ዘመቻው ለተሰለፉ የሰራዊት አባላት ቤተሰቦች ነጻ የትምህርት ዕድል ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ዛሬ ባካሄዱት ውይይት የሀገርን ክብር ለማስጠበቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እንዲሆን የአንድ ወር ደሞዛቸውን 30 ነጥብ 5ሚሊየን ብር በላይ ሰጥተዋል።

ደም በመለገስ ለሰራዊቱ ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ‘’ በስራችን የተጣለብንን ኃላፊነት በሚገባ በመወጣት ለሀገራችን ያለንን ክብር እናሳያለን፤ የአካባቢያችንንም ሰላም ለመጠበቅ የበኩላችንን ኃላፊነት በመወጣት የፀጥታ መዋቅሮችን እናግዛለን’’ ብለዋል።

ወደፊትም በሚችሉት አቅም ሁሉ የሃገርን ሰላምና ህልውና ለማረጋገጥ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከሰሜን ወሎ አካባቢ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በወሎ ዩኒቨርሲቲ ለተጠለሉ ወገኖች ከ1ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ቁሳቁሶችንና ምግቦችን በድጋፍ መስጠቱን የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጄይላን ወሊዪ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መንግስቱ ኡርጌ÷ የዘማቾችን ልጆችና ቤተሰቦች የትምህርት ዕድል ለመስጠት ሁኔታዎችን ለመለየት መመሪያ የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.