Fana: At a Speed of Life!

ተዘግቶ የቆየው የአዲስ አበባ ጎጃም መንገድ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ክፈት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በከባድ የቋጥኝ ድንጋይ መንሸራተት ምክንያት ተዘግቶ የቆየው የአዲስ አበባ ጎጃም መንገድ በከፊል ተጠግኖ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ለትራንስፖርት ክፍት ሆኗል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በሚወስደው መንገድ ዓባይ በረሃ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ልዩ ስሙ ፍልቅልቅ በሚባለው ስፍራ ላይ ያጋጠመውን ከባድ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ ሙሉ በሙሉ ክፍት ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው።

ችግሩን ለመፍታት አሰቸኳይ ጥገና የሚያደርግ ግብረ ሃይል ፣ በርካታ ማሽነሪና የሰው ሀይል በስፍራው ከሚገኘው አሰቸኳይ ጥገና ቡድን ጋር በጋራ በማሰማራት ፣ በተደረገው ጥረት መንገዱን፣ የዘጋውን ቋጥኝ ድንጋይ በደማሚትና በማሽነሪዎች በመታገዝ የመንገዱን ዋና ክፍል፣ በከፊል ነፃ ለማድረግ ተችሏል።

ይህን ተከትሎም ከዛሬ ምሽት ጀምሮ አንድ መኪና ከግራና ከቀኝ በየተራ ተሽከርካሪዎች ማስተላለፍ ይጀምራል።

የመንገዱን ቀሪ ክፍል ከዘጋው ቋጥኘ ድንጋይ ነጻ ለማድረግና መስመሩን ወደ ነበረበት ለመመለስ ሲባል የትራንስፖርት ፍሰቱን ለሰዓታት በመዝጋትና በመክፈት ቀሪ ስራዎቹ እንደሚከናወኑ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አሳስቧል።

በአካባቢው (በአባይ በርሃ) መንገድ ላይ ለቀናት የቆሙ በርካታ ተሽከርካሪዎች በመኖራቸው የትራፊክ ፍሰቱ እስኪቃለል በሁለቱም አቅጣጫ ከሚገኙ ከተሞች ጉዞ ያልጀመሩ አሽከርካሪዎች ነገ ባይንቀሳቀሱ ይመከራል።

እንደሚታወቀው የአባይ በረሃ አካባቢ የሚንሸራተት ጠመዝማዛና ናዳ የሚበዛበት በመሆኑና በዚሁ ስፍራ ከወትሮ የተለየ ግዙፍ ናዳ መከሰቱ ስራውን እጅግ አክብዶታል።

ይሁን እንጂ ባለስልጣኑ በቀጣይ ቀናት ይህን ጥረቱን በመቀጠል የትራንስፖርት ፍሰቱን ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበረበት እንደሚመለስ አረጋግጧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.