Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች የሕልዉና ዘማች ቤተሰቦችን ሰብል የመንከባከብ ሥራ እያከናወኑ  ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞችና አርሶ አደሮች ለሕልውና ዘማች ቤተሰቦች ሰብል የመንከባከብ ሥራ እያከናወኑ ነው።

የዘማች ማሳን ሲያርሙ ያገኘናቸዉ አርሶ አደር ሆነልኝ አወቀ የሕልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል የመንከባከብ ሥራን አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ወጣት ዘነበ ሸቴ አሸባሪዉ የትህነግ ቡድን እንደ አረም ተነቅሎ እስኪወድቅ ድረስ ለዘማች ቤተሰቦች የሚያደርገውን እንክብካቤ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

የአባቶችን ታሪክ ለመድገም ግንባር ድረስ ሂዶ ለመፋለም ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል።

የዘማች ባለቤት ወይዘሮ እንየ ጌታሁን እየተደረገላቸዉ ባለዉ ድጋፍ ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ ወለላው ደርሶ እንደገለጹት በወረዳዉ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል የመንግሥት ሠራተኞች እና አርሶ አደሮችን በማስተባበር የእርሻ፣የዘርና የአረም ሥራ ተከናውኗል።

ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ800 ሺህ ብር በላይ ይሆናል ነዉ ያሉት።

ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበርም የዘር እጥረት ያለባቸውን የዘማች ቤተሰብ አባላት በመለየት የጤፍ ዘር ማዳረሳቸዉን ተናግረዋል።

በዚህም 40 ሄክታር መሬት በዘር እንዲሸፈን ተደርጓል ብለዋል። የሕልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስም ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ወለላዉ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.