Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ በበጀት አመቱ ሶስት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ስራ ማስጀመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት አመት በርካታ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ተጨማሪ ሶስት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

በበጀት አመቱ በወጪ ንግድና የሃገር ውስጥ ምርትን ከመተካት አንጻር 400 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በነበሩ ተግዳሮቶች ሳቢያ 247 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ማግኘቱን ገልጿል።

የእቅዱን 54 በመቶ ያሳካው ኮርፖሬሽኑ ለእቅዱ አለመሳካት በዋነኛነት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው ኮቪድ19 ሳቢያ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች በመቀዛቀዙ እና በሰሜኑ ኢትዮጵያ በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ ለሙሉ ስራ ማቆሙ እንደምክንያት ተጠቅሷል።

የኮቪድ19 ወረርሽኝ የሚሆኑ የመከላከያ ግብዓቶችን በማምረት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን ማዳን ተችሏል ተብሏል።

በበጀት አመቱ በዘርፉ ለ45 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ56 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን የኮርፖሬሽኑ ዋና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ ማሞ ተናግረዋል።

በዘንድሮው በጀት አመት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ቁጥር 13 ለማድረስ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፥ ሶስት ተጨማሪ ፓርኮችን አጠናቆ ወደ ስራ በማስገባት እቅዱን ማሳካት ተችሏልም ብለዋል በመግለጫቸው።

ከዚህ ባለፈም በበጀት አመቱ ከታቀዱና ውጤታማ ከሆኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ ኮርፖሬሽኑ የሚመራበት ሰነድም ተዘጋጅቷል ነው ያሉት።

ከዚህ ባለፈም ከፍሳሽ ማስወገድ ጋር በተያያዘ በ2013 በጀት አመት ሰፊ ስራ በመሰራቱ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ማዳን መቻሉ ተጠቁሟል።

በ2014 በጀት አመት ከወጭ ንግድ 362 የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ከተኪ ምርቶች 139 ዶላር ለማግኘት እየተሰራ ነው።

በሃይማኖት ኢያሱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.