Fana: At a Speed of Life!

የድባጤ ከተማ ነዎሪዎች መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን የድባጤ ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪውን የሕወሓት ቡድንና ተላላኪዎቹን የሚቃወም እና ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።

ነዋሪዎቹ የውጭ እና የውስጥ ሀይሎች ኢትዮጵያን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ የሚያካሂዱትን እኩይ ተግባር እንዲያቆሙም ጠይቀዋል።

በድጋፍ ሰልፉ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች፣ የወረዳ አመራሮች፣ የሲዳማ ልዩ ኃይል፣ የፌዴራል የፖሊስና የወረዳው ፖሊስ አባላት፣ የሚሊሻ አባላት፣ የወረዳው የመንግስት ሠራተኞች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች።

ነዋሪዎቹ “ምዕራባውያን እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ”፤ “ሀገራችንን ለማዳን እንዘምታለን”፤ “አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ ወደኋላ አንልም”፤ “ባንዳዎች አፋችሁን ያዙ”፤ “ኢትዮጵያ ትቅደም፤ ጁንታው ይውደም” የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

በሰልፉ ላይ የተገኙት የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ፥ ህብረተሰቡ በመተከል ዞን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን በአሸባሪው ጁንታ ተላላኪዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ላለው የመከላከያ ሠራዊት የጀመረውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ማጠናከር ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ወጣቶች ብሔራዊ ትንኮሳዎችን በማቆም ጁንታውንና የጁንታውን ተላላኪዎች ለመደምሰስ ዛሬም ነገም ከመንግስት ጎን እንዲሰለፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የድባጤ ወረዳ ነዋሪዎች እያደረጉት ካለው የድጋፍ ሠልፍ በተጨማሪ በወረዳው ለመከላከያ ሰራዊት የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የተካሄደ ሲሆን 981 ሺህ 278 ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የተገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.