Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10 ሺህ በላይ ገጀራ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10 ሺህ በላይ ገጀራ መያዙን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታወቀ፡፡
ገጀራው ትላንት ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ከማህበረሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት መርካቶ ጣና የገበያ ማዕከል ጎን አድማስ ህንፃ ውስጥ ነው የተያዘው፡፡
አዲሱን የጦር መሳሪያ ቁጥጥር አዋጅ በሚጻረር መልኩ ተከማችቶ የተገኘው ይህ ገጀራ ተይዞ ጠቅላላ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን የፖሊስ ጣቢያው ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኢኒስፔክተር ብርሃኑ አለሙ ተናግረዋል፡፡
የጦር መሳሪያውን ክምችት በመጠቆም ረገድ የህብረተሰቡ ትብብር ከፍተኛ ነበር ያሉት ምክትል ኢኒስፔክተርሩ÷የብሄራዊ ደህንነት ባለሙያዎችና የፖሊስ አባላትም ድርሻም የጎላ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡
አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በማሰራጨት ለሽብር አላማ ለማዋል ታሳቢ ያደረገ የጦር መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል ነው ያሉት፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወንጀለኛው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት ነው ማለታቸውን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሽብርተኛ ቡድኖችን ተልዕኮ ለመፈጸም በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ህዝቡ እና ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት እያደረገ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.