የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው ህወሓት ሀገር ለማፍረስ የሚያደርገው ጥረት በጸጥታ አካላት ይከሽፋል-ዶ/ር እንድሪያስ

By Melaku Gedif

August 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ጁንታ ሀገር ለማፍረስ የሚያደርገው ጥረት በጸጥታ አካላት ይከሽፋል አሉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ፡፡

የወላይታ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ከተለያዩ የጸጥታ አካላትና ባለድርሻዎች ጋር የስራ ሂደቱን በተመለከተ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

ዶክተር እንድሪያስ በዞኑ የሰላምና ፀጥታ ስራው እንዲሳካ ያደረጉ የጸጥታ አካላት በተለይ አሸባሪው ጁንታ በሀገሪቱ  ጦርነት በከፈተበት ወቅት አከባቢያችሁን በመጠበቃችሁ የዞኑ መንግስት ያመሰግናችኋል ብለዋል።

በየጦር ግምባሩ ለሀገራቸው የሚዋደቁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን ከማመስገን ባለፈ በተለያየ መንገድ ከጎናቸው መቆም ይኖርብናል ነው ያሉት፡፡

የዞኑ መንግሥት ከዚህ ቀደም ለመከላከያ ሰራዊት አባላት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

በጥላሁን ሁሴን

 

ወታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!