Fana: At a Speed of Life!

ሸኔ የአሸባሪው ህወሃት ተላላኪ የሆነ አሸባሪ የጥፋት ቡድን ነው – የጎሎልቻ  ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሸኔ የአሸባሪው ህወሃት ተላላኪ የሆነ አሸባሪ የጥፋት ቡድን ነው ሲሉ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ባሌ ዞን የጎሎልቻ ነዋሪዎች ገለጹ።

ከጃራ ከተማና አካባቢዋ የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ህዝባዊ ሰልፍ በማካሄድ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸው፥ አሸባሪዎቹን ህወሃትና ሸኔን አውግዘዋል።

ሰልፈኞቹ አሸባሪው ሸኔ ከህወሃት የሽብር ቡድን ጋር ጥምረት በመፍጠር ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደረገው እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ኮንነዋል፡፡

“ህወሃትና ሸኔ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ናቸው፣ ሸኔ የህወሃት ተላለኪ የጥፋት ቡድን ነው፣ በሉዓላዊነታችን አንደራደርም ታሪክም ይመሰክራል” የሚሉ መፈክሮችን በማስተጋባት አሸባሪ ቡድኖቹን አውግዘዋል ።

በተጨማሪም “መከላከያ ሰራዊት የሉዓላዊነት ምልክት ነው፣ ለሀገራችን የምንሰስተው ቁሳዊ ንብረትም ሆነ ህይወት የለም” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ለመከላከያ ሰራዊት አጋርነታቸውን ገልጸዋል ።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የሰልፉ ተሳታፊዎች እንዳሉት፥ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን ሲያፍን፣ በኦነግ ስም በርካታ ወጣችና ንጹሃንን ሲረሽን ከነበረው ህወሃት ጋር የሚሰራ ማንኛውም ኃይል ተቀባይነት የለውም።

አሸባሪዎችን መዋጋት የዜጎችን በነጻነት የመኖር ህልውናን ከማረጋገጥ በተጓዳኝ የሀገርን ሉዓላዊነት የማስቀጠል ጉዳይ በመሆኑ በሙሉ ልብ የሽብር ቡድኖችን እንደሚታገሉ ገልጸዋል፡፡

ሀገርን የማዳን ዘመቻው በስኬት እንዲጠናቀቅ ስንቅ በማዘጋጀት፣ ደም በመለገስ እየተሳተፉ እንደሆነ ገልጸው፤ በቀጣይ የህይወት መስዋዕትነት እስከመክፈል የሚደርስ አስተዋጽኦ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የጎሎልቻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ጆብራ በበኩላቸው፥ ነዋሪው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን አጋርነትና ለአሸባሪ ቡድኖቹ ያለውን ተቃውሞ በመግለጽ ለአገራቸው ያላቸውን ክብር እንዳሳዩ ጠቅሰዋል።

ህብረተሰቡ ልጆቹ በፈቃደኝነት መከላከያን እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ያስታወሱት የምስራቅ ባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደም ቃሲም፥ ከዚህ በተጓዳኝ ደም በመለገስ፣ ስንቅ በማዘጋጀት፣ ለእርድ የሚሆኑ ሰንጋዎችና ፍየሎችን በመለገስ እየተሳተፈ ይገኛል  ብለዋል።

የህልውና ዘመቻው በድል እስኪቋጭ ድረስ ህብረተሰቡ እያደረገውን ያለው ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁት ደግሞ የኦሮሚያ እርሻና ተፈጥሮ ኃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ናቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.