Fana: At a Speed of Life!

በራያ ግምባር ለተሠለፈው ሠራዊት 18  ሠንጋዎች ፣122 በጎችና 7 ፍየሎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ እና የሰሜን ሸዋ ዞን የባሶና ወረና ወረዳ እንዲሁም የደሴ ከተማ ህዝብ በራያ ግምባር ለተሠለፈው ሠራዊት 18  ሠንጋዎች፣122 በጎችና 7 ፍየሎችን  አበርክተዋል።

የማዕከላዊ ዕዝ ም/አዛዥ ለሎጀስቲክስ ብ/ጀ ሻምበል ፈረደ፥ሕዝቡ ከመከላከያ ጎን በመቆም ላሳየው ቁርጠኝነትና አብሮነት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የደሴ ከተማ  ም/ከንቲባ አቶ ሰኢድ የሱፍ በበኩላቸው፥በአሁኑ ሰአት10 ኩንታል ደረቅ ሬሽንና 89 በጎችን በማቅረብ ደጀን ከሆነው ህዝብ የሚጠበቀውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የደሴ ከተማም  84 ሚሊየን ብር በማሰባሰብና አቅርቦት በማሟላት ከሠራዊቱ እስከ መጨረሻው አብሮነታችን ይቀጥላል ብለዋል።

የወሎ ዩኒቨርስቲ ኢንተርፕራይዝ አስተባባሪ አህመድ እሸቱ፥የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ግምባር ላይ ለተሰለፈው ሀይላችን ከኢኮኖሚያዊ እገዛ አልፎ ህይወት እስከመስጠት የተዘጋጀ ፣ በሀገሩ የማይደራደር ደጀን ህዝብ  ነው ያለው ብለዋል።

የሀገርን ሰላም ለማሳጣት የሚፍጨረጨሩ ሀይሎችን ቅስማቸውን ለመስበር ህዝባችን አንድነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.