Fana: At a Speed of Life!

በሀረር የኦሮሞ አርቲስቶች ማህበር ተመሠረተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረር የኦሮሞ አርቲስቶች ማህበር መመስረቱ ተገለፀ፡፡
ማህበሩ በወጣት እና አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች አማካኝነት መመስረቱም ነው የተገለጸው።
በምስረታ መድረኩ ላይ የሀረሪ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚልኬሳ አህመድን ጨምሮ በኦሮሞ ሙዚቃ አንጋፋ የሆኑት አርቲስት መሀመድ ጠዊል ኤሌሞ አሊ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
በርካቶች ህይወታቸውን ከፍለው ዛሬ ያደረሱትን የኦሮሞ ባህልና ኪነ ጥበብ÷ የዛሬው ትውልድ ተቀብሎ ወደ ፊት ለማስቀጠል የማህበሩ መመስረት የኦሮሞ ህዝብን የሚያኮራ መሆኑን ነው የማህበሩ መስራቾች የተናገሩት፡፡
በቲያ ኑሬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.