Fana: At a Speed of Life!

የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት የዶናልድ ትራምፕን የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ ተቹ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ የዶናልድ ትራምፕን የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ ኢ ፍትሃዊ ነው ሲሉ ተችተውታል።

ፕሬዚዳንቱ የሰላም እቅዱን “የምዕተ ዓመቱ ኢ ፍትሃዊነት” ሲሉ ገልጸውታል።

የሰላም እቅዱን አስመልክተው ባደረጉት ንግግርም ፍልስጤም የስምምነቱ ርዕሰ ጉዳይ አይደለችም፤ ይህም ኢ ፍትሃዊነት ነው ሲሉ እቅዱን አጣጥለውታል።

ዶናልድ ትራምፕ ከቀናት በፊት “ወሳኝ” ነው ያሉትን የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የሰላም እቅዱ እየሩሳሌምን የእስራኤል አይነኬ ከተማ አድርጎ የሚያስቀጥልና ለእስራኤል የሰፈራ ፕሮግራም እውቅና የሚሰጥ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል።

በቀጣይ ሁለት ሳምንታትም የፍልስጤሙ ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ በፀጥታው ምክር ቤት፥ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተገኙበት በሰላም እቅዱ ዙሪያ ንግግር
እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.