ስፓርት

ኢትዮጵያ ከዓለም አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

By Amare Asrat

August 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢስ) በኬኒያ ናይሮቢ ሲካሄድ በቆየው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡

በውድድሩ ኢትዮጵያ ሶስት ወርቅ፣ ሰባት ብር እና ሁለት የነሃስ በድምሩ አስራ ሁለት ሜዳልያዎችን አግኝታለች፡፡

በዚህም ኬንያን፣ ፊንላንድንና ናይጄሪያን ተከትላ ከዓለም አራተኛ ደረጃን በመያዝ ሻምፒዮናውን ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡