Fana: At a Speed of Life!

ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ በሃሰተኛ ሰነድ ለማውጣት የሞከሩት ተጠርጣሪዎች ፍ/ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ በሃሰተኛ ሰነድ ወደሌላ አካውንት በማዛወር ምዝበራ ለመፈፀም የሞከሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍር ቤት አራዳ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ፖሊስ በበኩሉ ለተጨማሪ ምርመራ ሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በዋለው ችሎት ፖሊስ የጠየቀውን የሰባት ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ምርምራው እንዲጠናቀቅ አዟል፡፡

በተጨማሪም የምርምራ ውጤቱን ለመጠበቅ ለነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ኢብኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.