Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስቴር ሠራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችና አመራሮች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
የገንዘብ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችና አመራሮች ዛሬ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ባደረጉት ውይይት÷ የወር ደመወዛቸውን ከ50 እስከ 100 ፐርሰንት ለመከላከያ ሠራዊት ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
 
የሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ÷ እናቶቻችንና አባቶቻችን ሉዓላዊነቷንና ክብሯን አስጠብቀው ያስረከቡን ሀገራችን በውስጥና በውጭ ወራሪ ኃይሎች እንዳትደፈር ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ ሁኖ በጋራ መቆም ይገባል ብለዋል፡፡
 
አመራር እና ሠራተኞች በየግንባሩ እየተፋለሙ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣የክልል ልዩ ሃይሎችና ሚሊሻ አባላት በደም ልገሳ፣ በገንዘብና በሞራል ድጋፍ በማድረግ የበኩላችንን ድራሻ እየተወጡ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡
 
በተጨማሪም ይህንን የህልውና ዘመቻ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ለሀገሩ ያለውን ፍቅር በተግባር ሊያሳይ ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.