Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ቡድን በርካቶችን ለጦርነት ማሰለፉ በትግራይ ህዝብ ላይ ዘር እንዳይተርፍ ያለውን ፍላጎት እንደሚያሳይ ምርኮኞች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በርካቶችን ለጦርነት ማሰለፉ በትግራይ ህዝብ ላይ ዘር እንዳይተርፍ ያለውን ፍላጎት እንደሚያሳይ የተማረኩ የአሸባሪው ቡድን ወታደሮች ተናገሩ።

ቡድኑ እያንዳንዱ ትግራዋይ ልጆቹን ለጦርነት እንዲያበረክት የሚያስገድድ ሲሆን÷ ልጆች የሌላቸው ወላጆች ራሳቸው እንዲዘምቱ ካልሆነ የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍሉ እንደሚያደርጉ ምርኮኞቹ ገልጸዋል።

ለትህነግ ስውር የስልጣን አላማ በርካቶች እየረገፉ ሲሆን÷ የተማረኩትም በግዳጅ በቡድኑ ዓላማው ወዳልገባቸው ጦርነት መግባታቸውን በወሎ ግንባር ቆይታ ላደረገው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የጋዜጠኞች ቡድን ተናግረዋል።

ምርኮኞቹ በአማራ ክልል ወረራ የፈፀመው የትህነግ ቡድን ሲመታ መሪዎች ጥለዋቸው መሄዳቸውን ጠቅሰው÷ ይህም የድሃ ልጆችን በመማገድ ራስን ለማትረፍ የተሄደበት ስግብግብነት የቡድኑን ሽፍታነት ያሳያል ብለዋል።

በከሃዲው ባንዳ ብርጋዴር ጀኔራል ከበደ ፍቃዱ ስር የሻለቃ መረጃ ሀላፊ የነበረው ገብረመስቀል ገብረጊዮርጊስ ፍቃዱ የሚመራው ሀይል ቢደመሰስም ክዶናል፤ ይህም አሳዝኖናል ነው ያለው።

ከምርኮኞቹ ውስጥ 16 አመት ያልሞላቸው ህፃናትና ሴቶችም ይገኙበታል።

ህፃናቱ መማር በሚገባን ጊዜ ዓላማው ላልገባን ጦርነት ተዳርገናል፤ ጓዶቻችን አልቀዋል፤ ሁሉም ትግራዋይ በመንቃት ልጆቹን ወደጦርነት መላክ የለበትም ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.