Fana: At a Speed of Life!

አንዳንድ ሃገራትና ዓለምአቀፍ ተቋማት የያዙትን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያርሙ በተጠናከር መልኩ መታገል ይገባል – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ ሃገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የያዙትን የተሳሳተ ግንዛቤ በፍጥነት እንዲያርሙ ለማድረግ እስካሁን ከሰራነው በላይ ተጠናክረን ልንታገል ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ፥የአንዳንድ ሃገራትና ዓለምአቀፍ ተቋማት ሁለት መልክ ሲሉ አስፍረዋል።

አሸባሪው ህወሓት የአንዳንድ ሃገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያን የመጠምዘዣ እጅ ነው የምንለው በምክንያት ነው ብለዋል።

አሸባሪው ህወሓት ተኩስ ማቆምን የሽንፈት ምልክት አድርጎ ሲወስድ፣ በኢትዮጵያ ሰራዊትና ህዝብ ወኔ ላይ ሲሳለቅ፣ በእብሪት ተሞልቶ  ንፁሀንን በመጨፍጨፍ ወደ አጎራባች የአማራና የአፋር አካባቢዎች ለመስፋፋት በርካታ ጥቃቶችን ሲሰነዝር እንደነበር አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም ህፃናትና ሴቶችን በጅምላ ሲጨፈጭፍ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ዝምታን የመረጡ ሃገራትና ዓለምአቀፍ ተቋማት በዚህ ሰዓት ከየአቅጣጫው የሚያሰሙት የተኩስ አቁም ጥሪ፣ የከሀዲ ድርጅቱን ህይወት በማራዘም በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያን የመምራት ድብቅ አጀንዳቸውን ገሀድ ያወጣ ተግባር ሆኗል  ብለዋል።

በመሆኑም መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዚህን የእናት ጡት ነካሽ ቡድን አረመኔያዊ ድርጊት ለማጋለጥና አንዳንድ ሃገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የያዙትን የተሳሳተ ግንዛቤ በፍጥነት እንዲያርሙ ለማድረግ  እስካሁን ከሰራነው በላይ ተጠናክረን ልንታገል ይገባልም ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.