ጠ/ሚ ዐቢይ ከአዲሱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ

By Tibebu Kebede

August 23, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአዲሱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት ጋር በስልክ ተወያዩ።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ከዚህ ባለፈም የሁለቱን ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ቃል መግባታቸውንም አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!