Fana: At a Speed of Life!

የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርን በዘላቂነት ለማስቀጠል ቁርጠኛ አቋም እንዳለው የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ ቦርድ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመዲናዋ የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርን በዘላቂነት ለማስቀጠል ቁርጠኛ አቋም እንዳለው የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ ቦርድ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት  የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ ቦርድ እንዲቋቋም መወሰኑ ይታወቃል።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥መርሃ ግብሩ ተማሪዎችን ከማገዝ ባሻገር በከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃ ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።

ከዚህ ባሻገር በአዲስ አበባ ከተማ እና ዙሪያ በሚገኙ አርሶ አደሮች መካከል የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ነው የተባለው።

መርሃ ግብሩ በሀገር አቀፍ ደራጃ ተግባራዊ መደረግ እንደሚገባው የገለጹት ወይዘሮ ፍሬዓለም ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት።

በዚህ መሰረትም ፖለቲከኞች፣ ባለሃብቶች፣ ወላጆች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለመርሃ ግብሩ ቀጣይነት እና መሻሻል የበኩላቸውን  አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ቦርዱ መርሃ ግብሩን  በዘላቂነት በማሻሻል ለመላ ሀገሪቱ የሚሆን ተሞክሮ የመቀመር እቅድ እንዳለው ነው  ምክትል ሰብሳቢዋ የተናገሩት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመርሃ ግብሩ በዘንድሮው ዓመት ለ600 ሺህ ተማሪዎች ዩኒፎርምን ጨምሮ የተለያዩ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ያቀረበ ሲሆን፥ 300 ሺህ ተማሪዎችን ደግሞ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር ተጠቃሚ አድርጓል።

በትዕግስት ስለሺ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.