Fana: At a Speed of Life!

ዕድሜያቸው ከ35 በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ 19 ክትባት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ዕድሜያቸው ከ35 በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ 19 ክትባት በመንግስት ጤና ጣቢያዎች ሊሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የጤና ቢሮው ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ካለፉት 4 ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ በኮቪድ 19 የመያዝ መጠን ፤ በጽኑ የሚታመሙ ሰዎች ፤ እንዲሁም በበሽታዉ ምክኒያት ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል : :

ይህም በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የታየውን የወረርሽኙ 3ኛዉ ማአበል በከተማችን የመታይት አዝማሚያ ያሳያል ብለዋል : :

የኮቪድ 19 ክትባትን መስጠት ወረርሽኙን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን÷ በኮቫክስ ፋሲሊቲ አማካይነት ወደ ሀገራችን የሚገቡትን ክትባቶች በየደረጃዉ ላሉ በስራ ባህሪያቸዉ ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋለጭ ለሆኑ የጤና ባለሙያወች ፤ እድሜቸዉ ከ65 አመት በላይ ለሆኑ እና እድሜቸዉ ከ 55 – 64 የሆኑና ተጓዳኝ የጤና ችግር ላለባቸዉ ብቻ ቅድሚያ እንዲያገኙ ሲደረግ መቆቱን ጠቅሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በለጋሽ ሀገራት እገዛ የተለያዩ ክትባቶች ወደ ሀገራችን እየገቡ እንደሚገኙና እስካሁንም አስትራዜኒካ ፤ ሲኖፋርምና ጆንሰን ጆንሰን የሚባሉ ክትባቶች አገልግሎት ላይ እየዋሉ ይገኛሉ ብለዋል : :

የክትባቶቹ መጠሪያ የተለያየ ቢሆንም በደህንነታቸዉና ፍቱንነታቸዉ፣ የወረርሽኙን ስርጭት ከመቆጣጠርና በወረርሽኙ ሊደርስ የሚችለዉን የከፋ ህመምና ሞት ከመከላከል አንጻር ሁሉም ክትባቶች ተመሳሳይ ዉጤት ያላቸዉ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም ማህበረሰቡ ያለምንም ስጋት ወደ መንግስት ጤና ጣቢያዎች በመሄድ ክትባቱን በነፃ ያለምንም ክፍያ በመዉሰድ ራሱንና ቤተሰቡን ከአስከፊ ወረርሽኝ እንዲጠብቅም ዶክተር ዮሐንስ ማሳሰባቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል: :

በዚህ ዙር የሚሰጠው ክትባት ከዚህ በፊት ክትባቱን ያልወሰዱ ከ1ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሆኑ ገልፀው÷ እድሜቸዉ 35 ዓመት የሆኑ: እድሜቸዉ ከ 18 አመት በላይ የሆኑና ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸዉ ሰዎች ክትባቱን ለመስጠት ታስቧል፡፡

በተጨማሪም በስራ ባህሪያቸዉ ተጋላጭ ናቸዉ ተብለዉ የተለዩ ከ105 በላይ ለሚሆኑ የመንግስትና የግል ተቋማት ክትባቱን ለመስጠት መታቀዱንም ገልጸዋል : :

በተጨማሪም ኃላፊው ክትባቱን መዉሰድ ወረርሽኙን ለመከላከል አንዱ ዘዴ ቢሆንም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ ዘዴዎችን መተግበር አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል : :

ህብረተሰቡ ክትባቱ የሚሰጠዉ በነፃ መሆኑን አዉቆ ምንም አይነት ክፍያ የሚጠይቅ አካል ካለ ለጤና ተቛሙ ሀላፊዎች ወይም በአቅራቢያዉ ለሚገኝ የህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ አሳስበው ቢሮው ጉዳዩን ተከታትሎ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ተናግረዋል : :

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.